Saturday, September 21, 2024
spot_img

በምሥረታ ላይ የሚገኙት ራሚስ እና ዛድ የተሰኙት ወለድ አልባ ባንኮች መዋሃዳቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― በምሥረታ ላይ የሚገኙት ራሚስ እና ዛድ የተሰኙት ወለድ አልባ ባንኮች መዋሓዳቸው ተሰምቷል፡፡ ባንኮቹ የተዋሃዱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠው የአምስት መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል መመስረቻ ካፒታል ጊዜ ከማለቁ በፊት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠው ገደብ ከተነሳ በኋላ አዳዲስ ባንኮች መመስረት የሚችሉት በ5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ሲሆን፣ ከገደቡ በፊት ከሆነ ግን በ500 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ የቻሉ ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።

ራሚስ እና ዛድ የተሰኙት ወለድ አልባ ባንኮች የተዋሃዱት፣ ለባንኮቹ የተሰጠው ገደብ ሊነሳ ከአንድ ወር በታች ጊዜ ሲቀረው ነው፡፡

በመዋሃድ ቀዳሚ የሆኑትን ራሚስ እና ዛድ የተሰኙ ወለድ አልባ ባንኮች ተከትሎ ሌሎች አራት በምስረታ ላይ ያሉ ባንኮች ለመዋሃድ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን የፎርቹን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከተዋሃዱት ወለድ አልባ ባንኮች መካከል ራሚስ የተሰኘው ባንክ፣ በመስከረም 2012 የአክሲዮን ሽያጭ ጀምሮ 400 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መመሰብሰቡ ሲነገር፣ ተጣማሪው ዛድ በበኩሉ ሰማንያ ሚሊዮን ብር ሰብስቧል መባሉን ዘገባው አክሏል፡፡

ሙሉ በሙሉ የወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ዘምዘም የተሰኘው ባንክ ወደ ገበያው በመግባት የመጀመሪያው ሆኖ ሥራ ከጀመረ ወራት ማስቆጠሩ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img