Friday, May 3, 2024
spot_img

የሱዳን ጀነራሎች በረመዳን ወር ‹‹ከጦርነት ለመጾም›› አልፈቀዱም

ለአስራ አንድ ወራት በከተማ ጦርነት ውስጥ የቆየችው ሱዳን፤ ከአንድ ቀን በኋላ በሚጀምረው የረመዳን ወር ‹‹ከጦርነት እንድትጾም›› በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የቀረበ ምክረ ሐሳብ እስካሁን በጦርነቱ ተፋላሚ ጀነራሎች ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ሱዳኖች በረመዳን ወር ጦርነቱን አቁመው የጥሞና ጊዜ ይውሰዱ በሚል ምክር ሐሳብ የቀረበው ዐርብ ነበር፡፡

የምክረ ሐሳቡ አቅራቢ ብሪታንያ የ14 አገራትን ድጋፍ ስታገኝ፤ ሩስያ ምክረ ሐሳቡን ድምጽ ባለመስጠት አልፋዋለች፡፡ ከዚህ የብሪታንያ ምክረ ሐሳብ አስቀድሞ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ሐሙስ እለት በተመሳሳይ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን ጋብ በማድረግ የረመዳንን እሴቶች እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከምክረ ሐሳቡ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመድ አምባሳደር፤ የቀረበውን ሐሳብ የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን እንደተቀበሉት ቢገልጹም ተፋላሚያቸው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ንጹሐን በሚገኙባቸው ሥፍራዎች ጥቃት እየፈጸመ እንዴት ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳለቸው ተናግረው ነበር፡፡ በአንጻሩ ትላንት ቅዳሜ ስለ ጉዳዩ መግለጫ ያወጣው በሌላኛው ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ምክረ ሐሳቡን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጧል፡፡

የሱዳን መደበኛ ጦር መሪ ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን እና ዳጋሎ ቀድመው ጦርነቱን በረመዳን ለማቆም በጎ ምላሽ የሰጡ ቢመስልም፤ ዘግየት ብለው በወጡ መረጃዎች ግን በተለይ የዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጦር ጦርነቱን ለመቀጠል ወስኗል፡፡ ይህንኑ በሱዳን መደበኛ ጦር ምክትል ኮማንደሩ ያሲር አል አታ በኩል አስታውቋል፡፡ ያሲር ባደረጉት ንግግር ሞራል፣ እሴት እና ሀይማኖት ከሌላቸው ሰዎች ጋር የሚቆም ጦርነት የለም ብለዋል፡፡ [አምባ ዲጂታል]

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img