Friday, May 3, 2024
spot_img

ሐና አርዓያስላሴ ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተመልሰዋል

ያለፉትን ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትን በዋና ሥራ አስፈጻሚ የመሩት ሐና አርዓያሥላሴ ቀድሞ በምክትል ኮሚሽነርነት የሠሩበትን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኮሚሽነርነት ለመምራት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሐና አርኣያሥላሴን ለኮሚሽኑ ኮሚሽነርነት የሾሙት ከትላንት ረቡዕ ጥር 8፣ 2016 ጀምሮ ነው፡፡

ሐና ከአሜሪካው ኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት በህግ ንድፈ ሃሳብ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ይዘዋል፡፡ ኮሚሽነሯ ወደዚህ ኃላፊነት ቦታ ከመምጣታቸው አስቀድሞ፤ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚነት በጠቻመሪ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም ሠርተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img