Friday, May 3, 2024
spot_img

የአማራ ክልል ህወሓት ‹‹ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል›› አለ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ሚያዝያ 9፣ 2016 – የአማራ ክልላዊ መንግሥት ህወሓት ‹‹ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል›› ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

የክልሉ መንግሥት በመግለጫው ‹‹ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው›› ነው ያለው ሕወሓት፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ጥሷል ሲል ከሷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት ህወሓት ‹‹ወረራ›› ፈጽሞባቸዋል ያላቸው አካባቢዎች የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ናቸው፡፡ የክልሉ መንግሥት በእነዚህ አካባቢዎች ሕወሃት የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት ‹‹በኃይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈፀም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈፀመባቸው›› ናቸው ሲልም ድርጅቱን ወንጅሏል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት በመግለጫው ሕወሓትን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ ‹‹በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ›› የጠየቀ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ‹‹ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመሆን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መሆኑን›› ይታወቅልኝ ብሏል፡፡

የአማራ ክልላዊ መንግሥት በሕወሓት ተፈጽሟል ያለውን ‹‹ወረራ›› በተመለከተ ከሕወሃት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img