Friday, May 3, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ አንድ ትሪሊዮን ብር ተሻገረ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ የካቲት 1፣ 2015 – የመንግሥታዊው ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን አንድ ትሪሊዮን መድረሱን ፕሬዝዳንቱ አቶ አቤ ሰኖ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ የ2015 የግማሽ ዓመት አፈጻጸሙን በተመለከተ በተሰጠው ማብራሪያ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 978.9 ቢሊዮን ብር መድረሱን ኃላፊዎቹ ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ይህም ከቀዳሚው ዓመት በ14 በመቶ ብልጫ ያሳየ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንገድ ባንክ አጠቃላይ የብድር ክምችት 975.7 ቢሊዮን ብር የደረሰ በመሆኑ፣ የብድር ክምችቱም በሒሳብ ዓመቱ ትሪሊዮን ብር ይሻገራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባንኩ በ2015 የሒሳብ ዓመት 2.2 ሚሊዮን ብር አዲስ ደንበኞች የቁጠባ ሒሳብ የከፈቱ ሲሆን፣አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 1,879 ማድረስ መቻሉን በዚሁ የግማሽ ዓመት ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ሲቢኢ ኑር (ከወለድ ነፃ አገልግሎት) ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ቁጥርም 130 የደረሱ ሲሆን፣ በ1,815 የባንኩ ቅርንጫፎችም ለዚህ አገልግሎት የተመደቡ መስኮቶች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img