Saturday, May 4, 2024
spot_img

የአይኤምኤፍ ባለሥልጣናት በቀጣይ ሳምንታት ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ጥር 3፣ 2016 – የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ሰዎች በቀጣይ ሳምንታት ወደ አዲስ አበባ በማምራት ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡

የገንዘብ ተቋሙ ድርጅት ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡበት ትክክለኛ ቀን ባይታወቅም፤ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የሚኖራቸው የአዲስ አበባ ቆይታ ግን ብርን በማዳከም ዙርያ የሚያጠነጥን መሆኑን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡

የአይኤምኤፍ ሰዎች አሁን ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩት በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍ የሚያስችል የውይይት ደረጃ ላይ በመድረሳቸቸው መሆኑንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ቀደም በወጡ መረጃዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከአይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ንግግር እያደረጉ እንደሚገኙ ተነግሮ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና የአይኤምኤፍ ሰዎች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ይነጋገሩበታል የተባለው ብርን የማዳከም ጉዳይ ለበርካታ ጊዜ ሲያከራክራቸው የቆየ ሲሆን፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ አለበት የሚባለውን መንግሥትንም አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ጉዳይ ስለመሆኑ ይነሳል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመደበኛ ምንዛሬ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ56 ብር ሲመነዘር፤ በአንጻሩ በትይዩ ወይም በጥቁር ገበያ እጥፍ ደርሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img