Saturday, May 4, 2024
spot_img

አልበሽር የነበሩበት እስር ቤት በመሰበሩ ወደ ጦሩ ሆስፒታል እንደተዘዋወሩ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ሚያዝያ 18፣ 2015 – የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሽር የነበሩበት እስር ቤት በመሰበሩ ወደ አገሪቱ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደተዘዋወሩ ተነግሯል፡፡ የአገሪቱ ጦር ዛሬ እንዳስታወቀው፤ የነበሩበት እስር ቤት እየተካጌደ በሚገኘው ጦርነት ምክንያት በመሰበሩ አልበሽርን ጨምሮ 30 እስረኞች ወደ አሊያ ሆስፒታል ተዘዋውረዋል፡፡

አሁን ወደ አገሪቱ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የተዘዋወሩት አልበሽር ከዚህ ቀደም ይገኙበት የነበረው በሰሜናዊ ካርቱም በሚገኘው ኮበር በሚባል እስር ቤት ነበር፡፡ የኮበር እስር ቤት ባለፈው እሁድ ተሰብሮ በሺሕዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡

በአገሪቱ ጦር መሪ ጀነራል አል ቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ዳጋሎ መካከል በሱዳን የተነሳው ጦርነት በኮበር እስር ቤት ያመለጡትን ጨምሮ ለሌሎች 25 ሺሕ በወንጀል ተከሰሱ ሰዎች ማምለጥ ሰበብ ሆኖ ካርቱምን ሕግ አልባ መሬት እነንዳደረጋት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

አሁን ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ተዘዋውረዋል የተባሉት ሱዳን ለበርካታ ዓመታት የመሩት አልበሽር፤ ከሥልጣናቸው በሕዝባዊ ተቃውሞ የዛሬ አራት ዓመት በዚህ ወር ነበር፡፡ አልበሽር በርካታ ክሶች ቀርቦባቸው በአገሪቱ ፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img