Saturday, May 18, 2024
spot_img

ወሰን ማካለል በተደረገባቸው አካባቢዎች የት/ት አሰጣጥ ሒደትና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት ይቀጥላል ተባለ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ነሐሴ 11 2014 ― በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ከልል ወሰን ማካለል በተደረገባቸው አካባቢዎች የትምህርት አሰጣጥ ሂደትና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት እንደሚቀጥል የገለጹት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው፡፡

ከንቲባዋ ይህን ያሉት ትላንት ነሐሴ 10 በአዲስ አበባ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ማካለል ላይ በሁለቱ ወገኖች የተደረሰ ስምምነት ላይ ከተካሄደው የህዝብ ውይይት በኋላ ነው፡፡

ወይዘሮ አዳነች በማኅበራዊ ሚዲያ በተነበበ ማስታወሻቸው፤ ‹‹የግጭት አጀንዳ የመከነበት፤ የህዝቦች አስተዋይነትና አብሮነት ያሸነፈበት ቀን›› ያሉትን የትላንትናው ቀን ‹‹ታሪካዊ ነው›› ብለውታል፡፡

ከተቲባ አዳነች በማስታወሻቸው ውሳኔውንም ‹‹ታሪካዊ›› ያሉት ሲሆን፣ ከውሳኔው በኋላ የተለወጡ አዲስ ማከለሎችን ዘርዝረዋል፡፡ በዚህም ኦሮሚያም በሚያስተዳድርበት ፤አዲስ አበባም ስታስተዳድርበት በነበረው ቦታ እንድትቀጥል መወሰኑን ያመለከቱት ወይዘሮ አዳነች፤ በኦሮሚያ ውስጥ በመግባት በርቀት በአዲስ አበባ ተገንብተዋል ካሏቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ኮየፈጨ፤ ቱሉዲምቱ በከፊልና ጀሞ ቁጥር ሁለት የሚገኙበትን ወደ ኦሮምያ ተካሏል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኦሮምያ ክልል ገንብቶታል ያሉትን የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ ከፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞች ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለሉ በማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል፡፡

ከዚያ ውጪ ሁሉም ባለበት ቦታ እንዲያስተዳድር ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሳችን በእጅጉ አኩትሮናል ያሉት ከንቲባዋ፤ የአስተዳደር ወሰን አጥር አይደለም፡፡ በህዝቦች መሃከል አጥር ልናበጅ አንችልም ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ይህ የአስተዳደር ወሰን በሚነካባቸው አካባቢዎችም በአካባቢዎቹ የትኛውም አይነት መንግስታዊ አገልግሎት እንደማይቋረጥ፣ የአገልግሎትና የፀጥታ ስራዎች በሁለቱም ወገን በጋራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሠራ፣ በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንደማይቆሙና ይልቁንም በፍጥነት የሚጠናቀቁበት ሁኔታ ልዩ ክትትልና ይደረጋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት ይቀጥላል የተባለ ሲሆን፣የሚሰጡ መንግስታዊ አገልግሎቶች ላይ ቋነን ምንም አይነት ተፅእኖ እንዳያሳርፍ እንደሚደረግ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ትላንት በተካሄደው ስብሰባ ከአዲስ አበባ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተወጣጡ የተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች፤ አባገዳዎች፤ የሃይማኖት አባቶች፤ አገር ሽማግሌዎችና የነዋሪዎች ተወካዮች መገኘታቸው ተገልጧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img