Saturday, May 18, 2024
spot_img

ብርን ከዶላር አንጻር የማዳከሙ እለታዊ አሠራር ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በቀደሙት ወራት ከነበረው ቅናሽ አሳየ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ የካቲት 25 2014 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የብር የምንዛሪ አቅምን በማዳከም የውጪ ንግድን ለማሳደግ በሚለው አሰራር ላይ ተመርኩዞ የሚያደረገው ብርን ከዶላር አንጻር የማዳከሙ እለታዊ አሠራር ከባለፈው ሳምንት ጨምሮ ቀድሞ ከነበረው ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በዚሁ መሠረት በቀጠለው አሠራር ባለፉት ወራት በተከታታይ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር በባንኮች ሲመነዘር በየቀኑ ከ5 እስከ 7 ሳንቲም ጭማሪ ሲያሳይ ቆይቷል፡፡

ነገር ግን ከባለፈው ሳምንት የካቲት 15 ጀምሮ ቀድሞ ከነበረው ጭማሪ በመቀነስ፣ ባለፈው አንድ ሳምንት በየቀኑ የ1 ሳንቲም ጭምሪ ብቻ እያሳየ መጥቷል፡፡ አምባ ዲጂታል ባካሄደው ቅኝት አንድ የአሜሪካ ዶላር ከየካቲት 15 በፊት በነበሩት ተከታታይ ሦስት ቀናት በባንኮች ሲመነዘር በየቀኑ የ6 እና የ7 ሳንቲም ጭማሪ ሲያሳይ ነበር፡፡

በባንኮች በሚካሄደው በዚሁ ምንዛሬ ቅናሽ ያሳየበት ምክንያት እስካሁን በይፋ ባይነገርም፣ በተያዘው ወር በወጡ መረጃዎች የብርን ዕለታዊ ዋጋ የማዳከም አሰራር የሚገመግም የዳሰሳ ጥናት በመንግስት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በጥናቱ ላይ በመመርኮዝም መንግስት ብርን በየዕለቱ የማዳከሙ ነገር ‹‹ይቀጥል›› ወይስ ‹‹አይቀጥል›› የሚለው ላይ ከውሳኔ ለመድረስ አቅዷል ነው የተባለው፡፡

ዕለታዊ የብርን የውጭ ምንዛሬ ተመን ከንግድ አጋር ሀገራት መገበያያ አንጻር በፍጥነት የማዳከሙ እርምጃ ከሁሉም የማክሮ ኢኮኖሚ መመዘኛዎች አንጻር የማያዋጣ ከሆነ ብሄራዊ ባንኩ ሌሎች አማራጮችን ለመከተል ይገደዳል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከ2012 ጀምሮ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚል ሥያሜ እየተገበረ የሚገኘው የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን አሰራር፣ የኢትዮጵያን ብር ትክክለኛ ዋጋውን እንዲያገኝ እና የወጪ ንግድን ለማሳደግ ይረዳል በሚል የሚያደርገው ነው፡፡

ዕለታዊው ፈጣን ምንዛሬን የማውረድ እርምጃ ከ2012 ተጀምሮ በተያዘው ዓመት 2014 እንዲያልቅ ታቅዶ ነበር፡፡ እርምጃውን ተከትሎ በ2012 መጀመርያ ላይ አንድ የአሜሪካን ዶላርን በባንክ ሲቀርብበት ከነበረው 29 ብር አሁን ዋጋው ወደ 50 ብር ከ79 ሳንቲም አድጓል። 

አሁን መንግስት እየተከተለ ያለው የምንዛሬ ተመን አሰራር የገቢ እቃዎችን ዋጋ በማስወደድ የዋጋ ንረትን የፈጠረ በመሆኑ የሚተች ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img