Saturday, May 18, 2024
spot_img

በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የብር የመግዛት አቅም ከአሜሪካን ዶላር አንጻር ከ20 ብር በላይ ሊዳከም እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ገፋፊነትና በኢትዮጵያ መንግሥት ይሁንታ እየተፈፀመ ነው በሚባለው የብርን የመግዛት አቅም የማዳከም ሂደት በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የብርን የመግዛት አቅም ከአሜሪካን ዶላር አንጻር አሁን ካለበት የ42 ብር፣ በ2024 በ64 ብር ከ84 ሳንቲም እንዲመነዘር ሊያደርገው እንደሚችል ስታንዳርድ ባንክ ይፋዊና ገለልተኛ በሆነ መንገድ አልተሠራም ባለው ጥናት ላይ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

ባንኩ ከዚህ በተጨማሪም የፈረንጆቹ 2021 ሲያልቅ አንድ የአሜሪካ ዶላር ባንኮች የሚሸጥበት ተመን 46 ብር ከ97 ሊሆን እንደሚችል፣ በ2022 እና 2023 መጨረሻዎች ላይ ደግሞ የአንድ ዶላር ምንዛሬ በ53 ብር ከ72 እና 58 ብር ከ23 እንደሚሆን አስቀምጧል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት አንድ የአሜሪካ ዶላር ይመነዘር የነበረበት ተመን በየቀኑ በሳንቲም ደረጃ እየጨመረ በግንቦት 2010 ከነበረበት 29 ብር ተነስቶ አሁን በያዝነው ሚያዚያ ወር 2013 42 ብር ደርሷል። ይህም የብር የመግዛት አቅም በ44 ነጥብ 9 በመቶ እንደቀነሰ ያመለክታል፡፡

በዚህ መሠረት የብር የመግዛት አቅም ማሽቆልቆል በዚህ ከቀጠለ የተባለው አሐዝ ላይ ቀድሞ መደረሱ እንደማይቀር ነው የተነገረው፡፡

መንግሥት የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም ዋና አላማው ወደ ውጪ የሚላክን ምርት ለመጨመርና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ሆኖም መንግሥት ይህን የፖሊሲ ርምጃ ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ ሞክሮት ምንም ዓይነት የሚጨበጥ ለውጥ አለማምጣቱን አንስተው አማራጭ ፖሊሲ እንደሚስፈልግ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img