Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሐዱ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የሆነው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ መታሠሩ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 17 2014 የአሐዱ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የሆነው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ መታሠሩ ተሰምቷል፡፡ ጋዜጠኛው የታሠረው በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 16፣ 2014 እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

የጋዜጠኛው ጠበቃ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ነገሩኝ ብሎ የኛ ቴሌቪዥን እንደዘገበው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ክብሮም ወደሚሠራበት የአሐዱ ራዲዮና ቴሌቪዥን በመሄድ በስራ ቦታው ሲያጡት ደውለው ቢሮ እንደሚፈለግ ገልጸውለት ከቢሮው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይዘውት ሄደዋል፡፡

ጋዜጠኛ ክብሮም ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፣ መርማሪ ፖሊስ ‹‹ጋዜጠኛውን ከፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ግኝኑነት አለው በሚል ወንጀል ጥርጥሬዋለሁ›› ማለቱን እንዲሁም ‹‹የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት ለዕኩይ አላማ እያዘጋጀ ነበር የሚል ጥርጣሬም እንዳለው አስረድቷል›› ሲሉ ጠበቃው ገልጸዋል ተብሏል፡፡

ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ በሚሠራበት አሐዱ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን የዜና ክፍል ኃላፊ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በጣቢያው በተመሳሳይ ጋዜጠኛ የሆነችው ልዋም አትክልቲ በደቡብ ወሎ ሐይቅ ከተማ የሕወሓት ታጣቂዎች መግባታቸውን እና ከተማዋን እየዘረፉ መሆኑን የሚገልጽ ዜና አሰናድታ አየር ላይ በማዋሏ በአዲስ አበባ ፖሊስ መታሰሯን ዘገባው አስታውሷል።

ከጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ጋር በተገናኘ የተሰየመው ችሎት ጉዳዩን በመመልከት ለጥቅምት 24፣ 2014 የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img