Monday, November 25, 2024
spot_img

የዩኬ መንግሥት በኢትዮጵያ ሦስት አካባቢዎች ላይ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 2፣ 2014 ― የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ በመላው ትግራይ ክልል እንዲሁም በ30 ኪሎ ሜትር ድንበር ላይ በሚገኙ አማራና በአፋር ክልሎች ላይ የሚገኙ አካባቢዎች መንገደኞች እንዳይጓዙ መክሯል፡፡

በትላንትናው እለት በወጣው ማስጠንቀቂያ ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው ያለው የዩኬ መንግስት፣ ውጊያው በፍጥነት የመዛመት አዝማሚያ እንዳለው በመጥቀስ ወደ ትግራይ እና 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ባሉ የአማራና የአፋር ድንበር ግዛቶች አንዳይጓዙ ብሏል፡፡

እንዲሁም በአማራ በአፋር ውስጥ ውጊያዎች እየተካሄዱባቸውና ሊካሄዱባቸው በሚችሉ ስፍራዎች ዜጎችና ሠራተኞች እንዳይጓዙ የመከረ ሲሆን፣ ከጠቀሳቸው አካባቢዎች መካከል በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን፣ ዋግ ኽምራ ዞን፣ አምባሰል፣ ተሁለደሬ እና ደሴ ወረዳዎች፣ እብናት፣ ከምከም፣ ላይ ጋይንት፣ ፋርጣ፣ ፎገራ፣ ደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳዎች፣ ዓዲ አርቃይ፣ በየዳ፣ ደባርቅ፣ ደባት፣ ወገራ፣ በላሰ፣ ጃናሞራ፣ ሳንጃ ወረዳዎች እና ሰሜን ጎንደር ዞን ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም በአፋር ክልል መላው ዞን 4፣ በዞን አንድ የጭፍራ ወረዳና ዳሎል፣ ኩኔባ፣ አባአላና በዞን 2 ሜጋሌ ይገኙበታል።

ለዜጎቹም በወታደራዊ እንቅስቃሴ አካባቢ ውስጥ ከሆኑ እና በደህና መውጣት ካልቻሉ፣ በቤት ውስጥ ለደኅንነታቸው አስተማማኝ በሆኑ ስፈራዎች ላይ እንዲቆዩና አካባቢዎቹን ለመልቀቅ የሚያስችሉዎ ሁኔታዎች በንቃት መከታተል እንደሚገባቸውም አስታውቋል።

ጦርነቱ እየተካሄደበት ካለበት ከሰሜን ኢትዮጵያ በተጨማሪ መረጋጋት አይታይባቸውም በተባለባቸው በጋምቤላ ክልል አራት ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ ምሥራቅ ወለጋ መንገደኞች እንዳይጓዙ መክሯል።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ሶማሌ ክልል የተወሰኑ ቦታዎች፣ በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ፣ ኢትዮጵያ ሶማሊያና ኬንያ በሚዋሰኑበት ድንበሮችም መንገደኞች እንዳይሄዱ ከተጠቀሱት ስፈራዎች ይገኙበታል።

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በኮንሶ ዞን እና በአካባቢው የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ ውጥረት መንገሱንና በመተከል ዞን የተከሰተውን የትጥቅ ጥቃትን ተከትሎ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውጥረቱ መፈጠሩንም ጠቅሶ ከሁኔታው እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በደቡባዊ ድንበር ከኬንያ በምትዋሰንበት ቦታ የአፈና ስጋት ስላለ ወደዚያም አካባቢ እንዳይሄዱ ምክር ተሰጥቷል።

አክሎም አሸባሪዎች በኢትዮጵያ ላይ ጥቃ ሊፈፅሙ እንደሚችሉም ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img