Monday, September 23, 2024
spot_img

በእስር ላይ በሚገኙት 3 ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ በሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች ላይ ለአራተኛ ጊዜ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ፍርድ ቤቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በሆነው በቃሉ አላምረው፣ በሚዲያው ላይ በተንታኝነት በሚሳተፈው ፋኑኤል ክንፉ እንዲሁም የ‹‹ኢትዮ ፎረም›› ጋዜጠኛ በሆነው አበበ ባዩ ላይ ነው።

የወረዳው ፍርድ ቤት ለዛሬ ነሐሴ 6፤ 2013 ቀጥሮ የነበረው፤ ፖሊስ ባለፈው ችሎት በተፈቀደለት አስር የምርመራ ቀናት ያከናወናቸውን ተግባራት ለመስማት ነበር።

ነገር ግን ፖሊስ ‹‹ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም›› በማለቱ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ አራት የምርመራ ቀናት መፍቀዱን የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አቶ ታደለ ገብረመድሀን ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳደር ዘግቧል፡፡

በዛሬው የችሎት ውሎ ከሦስቱ ጋዜጠኞች ጋር አብሮ ፍርድ ቤት በቀረበው አክቲቪስት ጸጋዘአብ ኪዳኔ ላይም፤ ፖሊስ ተመሳሳይ የምርመራ ቀናት እንደተፈቀደለት ጠበቃው አስረድተዋል። አራቱም ተጠርጣሪዎች በዛሬው ችሎት ለፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ መደረጉንም ጨምረው መግለጻቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img