አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 16፣ 2013 ― ከሁለት ዓመት በፊት በበዲስ አበባ ከተማ በወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ላይ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቤት እንዲሰጣቸው ውሳኔ አሳለፈ፡፡
በዛሬው እለት የተሰየመወ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 8ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት የ40/60 እጣ አወጣጥ ህገወጥ ነው ያለ ቢሆንም፣ ማህበራዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በሚል የቀድሞ እጣ ግን ባለበት እንዲጸና፣ እነዚህ ቅሬታ አቅራቢዎች ግን ቤት እንዲሰጣቸው ወስኗል ጠበቃቸው አቶ አንዱዓለም በውቀቱ ገልጸዋል፡፡