Friday, October 11, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ሊወጣ ነው መባሉን አስተባበለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሰኔ 8፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ‹‹የከተማ አስተዳደሩ የ20/80 እና የ40/60 የጋራ ቤት እጣ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ›› በሚል ያወጣው ዘገባ ‹‹ከእውነት የራቀ ነው›› በሚል ማስተካከያ እንዲያወጣ በመጠየቅ መረጃውን አስተባብሏል፡፡

ኮርፖሬሽኑ መረጃን የሚመለከታቸው አካላት ያልሰጡበት ነው ላለው ዘገባ፣ ጋዜጣው በአስር ቀን ውስጥ ማስተባበያ እንዲሰጥ የጠየቀ ሲሆን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ማስተባበያው ካልወጣ ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ እገደዳለሁ ብሏል፡፡

ሪፖርተር ባተመው ዘገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሁለት ሺሕ በላይ ቤቶችን ለዕጣ ማዘጋጀቱን ገልጾ ነበር፡፡ በተለይ በ1997 ተመዝግበው ላለፉት 16 ዓመታት በመጠባበቅ ላይ ያሉት ነዋሪዎች ይወጣል በተባለው ዕጣ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚካተቱም ነበር ዘገባው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img