Friday, May 3, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ላይ ርክክብ ያልተፈጸመባቸው የንግድ ቤቶች ወደ መኖሪያ ቤትነት እየተቀየሩ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰሞኑ የከተማ አስተዳደሩ በአንዳንድ ሳይቶች የሚገኙ የ40/60 የጋራ የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ ለንግድ የተዘጋጁ እና ለጨረታ እንደሚቀርቡ ሲጠበቁ የነበሩ የንግድ ቤቶችን እያፈረሰ በመገንባት ቅርፃቸውን በአፋጣኝ ወደ መኖሪያ ቤት የመቀየር ሥራ በሥፋት እየተከናወነ መሆኑን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡

በመሪ ሎቄ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር ይህ የንግድ ቤቶችን በፍጥነት ወደ መኖሪያ ቤትነት የመቀየር የግንባታ ሂደት እሑድን ጨምሮ በከፍተኛ ፍጥነት እንደሚከናወን ነው የተነገረው፡፡

የመሪ ሎቄ የ40/60 የመኖሪያ መንደር የካቲት 27፣ 2011 በያኔው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በነበሩት አቶ ዣንጥራር ዓባይና በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ በነበሩት አቶ ታከለ ኡማ በይፋ ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል አንዱ ነው።

እያንዳንዳቸው 13 ወለል ያላቸው 14 ብሎኮችን ያካተተው ይህ የመኖሪያ መንደር፣ በ2011 የካቲት ወር እጣ የደረሳቸው የዚሁ መንደር የቤት እድለኞች በዘንድሮ ዓመት የቤታቸውን ቁልፍ ተረክበው ኑሮ ለመጀመር አስፈላጊውን የግንባታ የመጨረሻ ምእራፍ ሥራም እያከናወኑበት ይገኛሉ፡፡

በዚሁ መንደር ከሚገኙት ብሎኮች መካከል ለንግድ ሥራ የተዘጋጁት ቤቶች በአሁኑ ወቅት ከውስጥ እየተከናወነ በሚገኝ ግንባታ ወደ መኖሪያ ቤት አገልግሎት እየተቀየሩ ስለመሆኑ ነው ሬድዮው በድረ ገጹ የዘገበው፡፡

በዚህ ሥራው በሚከናወንባቸው ብሎኮች በአጠቃላይ አስከ 80 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች ከንግድ ቤት ወደ መኖሪያ ቤትነት እየተቀየሩ ነው የተባ ሲሆን፣ ንግድ ቤቶቹን ወደ መኖሪያ ቤትነት ለመቀየር እየተከናወነ ባለው ሥራም ቀድሞ ለንግድ አገልግሎት ታስቦ የተሠራውን ግንባታ በማፍረስ እንደ አዲስ ከሕንጻው ውስጠኛ ክፍል ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።

በነዚህ የጋራ መኖሪያ መንደሮች የሚገኙ ቤቶች እጣ ከወጣባቸው ከ2 ዓመታት በላይ ተቀጥሮ እያለ እና ቤቶቹ በግልጽ ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገው ተሠርተው ሳለ በአፋጣኝ ወደ መኖሪያ ቤትነት የመቀየር ሥራው ለምን እንዳስፈለገ የአዲስ አበባ መስተዳድር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት እንዳልፈቀዱም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img