Thursday, October 10, 2024
spot_img

አፕል የአንዲት ተጠቃሚውን ስልክ ለመሥራት ወስዶ ፎቶዋን በማጋራቱ ሚሊዮን ዶላሮች ተቀጣ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― ግዙፉ አሜሪካዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ሠራተኛው ስልኳን ለማሠራት ያመጣች አንዲት ተጠቃሚ ፎቶን በማጋራቱ ድርጅቱ በርካታ ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል ነው የተባለው።

ስልኳን ለማሠራት ወደ አንድ የአፕል ሱቅ ያመራች ግለሰብ ግላዊ ፎቶዎች በፌስቡክና ሌሎች ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ ልክ እሷ እንደለጠፈችው ተደርገው መቀመጣቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ይህ ጉዳይ ወደ መገናኛ ብዙሃን ሲመጣ መጀመሪያ የአፕል ስም አልተጠቀሰም ነበር የተባለ ሲሆን፣ አሁን አፕል ጉዳዩን አምኖ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
በጉዳዩ ላይ መግለጫ የለቀቀው አፕል ‹‹የተጠቃሚዎቻችንን ግላዊ መረጃ መጠበቅን በጣም እናከብራለን፤ ሰዎች ስልኮቻቸውን ሲያሠሩ መረጃዎቻቸው እንዴት ሊጠበቁ ይችላሉ የሚለውን በተለመከተ ያወጣነው መመሪያ አለ›› ብሏል።

አፕል በጉዳዩ እጃቸው አለበት ያላቸውን ሁለት የስልክ ጥገና ሠራተኞች እንዳባረረ ተዘግቧል።

በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ስሙ እንዳይነሳ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ፔጋትሮን የተሰኘው ኩባንያ ለአፕል የካሳ ክፍያ በከፈለበት ወቅት ነው የግዙፉ ድርጅት ስም ይፋ የወጣው።

ሁኔታው አሜሪካ ውስጥ ስልክ ለጥገና ወደ ሱቅ መወሰድ የለበትም ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነላቸው ተነግሯል።

ከአሜሪካ ግዛቶች 20ዎቹ ‹ራይት ቱ ሪፔይር› የተሰኘው ረቂቅ ለውሳኔ አቅርበዋል። ረቂቁ አፕልን የመሳሰሉ ግዙፍ ድርጅቶች ስልክ ሲያመርቱ ለጥገና የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ለሦስተኛ ወገን ጠጋኞች እንዲሰጡ ያስገድዳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img