Monday, October 7, 2024
spot_img

የወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጠበቆች በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ሊተላለፍ ነው ያሉትን ዘጋቢ ፊልም በመቃወም ለፍርድ ቤት አቤት አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― በዚህ ሳምንት ዳግም ወደ ወህኒ የወረዱት የቀድሞ የፌዴሬሽን ክር ቤት አፈ ጉባኤ የወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጠበቆች በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተሠርቶ ሊተላለፍ ነው ያሉትን ዘጋቢ ፊልም በመቃወም ለፍርድ ቤት አቤት ማለታቸው ተነግሯል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የወይዘሮ ኬሪያ ጠበቃ ታደለ ገብረ መድኅን «እሳቸውን በተመለከተ ዶክመንታሪ እንዳይሠራ እና እንዳይተላለፍ አስቀድሞ ፍርድ ቤቱ እግድ እንዲሰጥ ነበር የጠየቅነው›› ያሉ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግም የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ውድቅ ሊደረግ ይገባል ብሎ ምላሽ ሰጥቶ ክርክር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 27፣ 2013 ቀጠሮ መስጠቱን የዘገበው ዶይቸ ቬለ ነው፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ መረጃ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በእነ አቶ ስብሓት ነጋ መዝገብ በተከሰሱ 43 ተከሳሾች የምስክርነት ቃል በትላንትናው እለት በዝግ እና ከመጋረጃ ጀርባ ማድመጥ ጀምሯል፡፡

ከዚህ ቀደም በአቃቤ ሕግ ምስክርነት ቀርበው የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በችሎቱ 43ኛ ተከሳሽ ሆነው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img