Friday, November 22, 2024
spot_img

መንግሥት በ20/80 አሠራር ከአልሚዎች ጋር በመተባበር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱ ተነገረ


አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥር 18 2014 ― ከዚህ በኋላ ለዜጎች ቤት እየገነባሁ ማዳረስ አልችልም ያለው መንግሥት፣ ከአልሚዎች ጋር በመተባበር 20/80 በተባለ አሠራር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱ ተነግሯል፡፡

ይተገበራል የተባለው ይህ አሠራር፣ ቤት ፈላጊዎችን ከአልሚዎች ጋር በማስተሳሰር የሚከናወን ሲሆን፣ ከወጪ 20 በመቶው በመንግስት እንዲሁም 80 በመቶው በአልሚዎች እንዲሸፈን ታስቧል፡፡

ይህንኑ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ደኤታ የሆኑት አቶ ሔኖስ ወርቁ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ሰኞ ጥር 16፣ 2014 የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ2014 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርት ላይ ግምገማ ባካሄደበት ወቅት ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ ሔኖስ ከሆነ ቤት ፈላጊዎችን ከአልሚዎች ጋር በሚያስተሳስረው በዚህ እቅድ፣ በርካታ አልሚዎችን ወደ ገበያው በማስገባት ተወዳዳሪ አድርጎ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ቤቶች እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡

የለማ መሬትና የፋይናንስ ችግር፣ የቴክኖሎጂ እጥረት፣ እንዲሁም ከዜጎች የመግዛት አቅም ውስንነት ጋር ተዳምሮ ቤት ማቅረብ ከባድ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የሪል ስቴት አዋጅ፣ አልሚዎች ተደራሽ የሆኑ ቤቶችን ለኅበረተሰቡ በስፋት ያደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

በሌላ መረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይጠናቀቁ ለማስተላለፍ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተነግሯል፡፡ እነዚህ ቤቶች የማጠናቀቂያ ዋጋቸው 19 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ሲነገር፣ የግንባታ ደረጃቸው በአማካይ 87 በመቶ መድረሱም ተመላክቷል፡፡

እነዚህ ቤቶች መሠረታዊ ግንባታ የተጠናቀቀላቸው ቢሆንም፣ የውኃ፣ የመንገድ፣ የውስጥ ለውስጥ ፍሳሽና መብራት መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ ሕንፃዎች ባለ18 ፎቅ በመሆናቸው አሳንሰር ያልተገጠመላቸውና እንዴት ይተላለፉ የሚለው ጥያቄ በመፍጠሩ ይኸው የዳሰሳ ጥናት ማስፈለጉ ነው የተገለጸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img