Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የሊቢያ ምርጫ ኮሚሽን የጋዳፊን ልጅ ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሠረዘ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 16፣ 2014 ― የሊቢያ የምርጫ ኮሚሽን የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅ የሆነው ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ከሳምንታት በኋላ በሀገሪቱ ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሠርዞታል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሰይፍ አል ኢስላም ጋዳፊን ጨምሮ በርካታ እጩዎችን ያገደው ህጋዊ ምክንያቶችን በመጥቀስ መሆኑ ነው የተነገረው።

አል ኢስላም አባቱ ጋዳፊ ሊቢያን በሚያስተዳደሩበት ወቅት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል እና በነፍስ ግድያ የሚፈለግ ሰው ነበር። በዚህ ሰበብ የጋዳፊ ልጅ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ከተሰማ በኋላ ውዝግብ ማስነሳቱ ሲነገር ሰንብቷል።

በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ሰኞ በተጠናቀቀው የሊቢያ ፕሬዝዳንት እጩዎች ምዝገባ ስልሳ ሰዎች ሊቢያን በፕሬዝዳንት ለመምራት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች የወንጀል ክስ የቀረበባቸው ዝነኛው ካሊፍ ሃፍታር ለምርጫ ለመወዳደር መመዝገባቸው በሀገሪቱ ውስጥ ውዥንብር ፈጥሯል። ነገር ግን ምርጫ ኮሚሽኑ ሃፍታርን ከፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ውጭ ያድርጋቸው አይድርጋቸው የታወቀ ነገር የለም።

የሊቢያ ወታደራዊ አቃብያነ ህግ የጋዳፊ ልጅ እና የሃፍታር በቀረበባቸው ክስ ላይ ተገቢ መልስ እስኪያቀርቡ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን በእጩነት ለማሳተፍ የሚያደርገውን ሂደት እንዲያቆም ጠይቀው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img