Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሑቲ ታጣቂዎች ፍርድ ቤት ትራምፕ እና ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን በሌሉበት ሞት ፈረደ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― በየመን የሑቲ ታጣቂዎች ፍርድ ቤት የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕንና የሳኡዲውን ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማንን በሌሉበት ሞት ፈርዶባቸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በነትራምፕ መዝገብ ተከሰው የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ከትላንት በስቲያ በአደባባይ በሞት እንደቀጣም ተዘግቧል፡፡

በሞት የተቀጡት ሰዎች ጠቃሚ መረጃ ለጠላት በማሾለክ የሑቲ ከፍተኛ የፖለቲካ መሪ የነበሩትን ሳሊህ አል ሳማድ እና ሌሎች ስድስት ሰዎች በሳኡዲ መራሹ የአየር ድብደባ እንዲገደሉ አድርገዋል በሚል የተከሰሱ ናቸው፡፡

ባለፈው እሑድ በአደባባይ ላይ በሞት የተቀጡት ዘጠኝ ሰዎች ፎቶና ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡

ሰዎቹ የተገደሉት በሰንአ ታህሪር አደባባይ ሕዝብ በተሰበሰበበት ነበር፡፡

በመዝገቡ ሰባተኛው ተከሳሽ የሳኡዲው ልኡል መሐመድ ቢን ሰልማን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሌሉበት ሞት እንደተፈረደባቸው የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ከፍርድ ውሳኔው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ግድያውን ያወገዙት ሲሆን፣ የአውሮፓ ኅብረት ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img