Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሱዳን እና ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት የትብብር ሥምምነት ተፈራረሙ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― ሱዳን እና ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት የትብብር ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የቀድሞው የሱዳን መሪ ኦማር አል-በሽር በዳርፉር ተፈጽመዋል በሚባሉ እና በሚከሰሱባቸው ወንጀሎች ከችሎት እንዲቀርቡ ለማድረግ አንድ ርምጃ ነው ተብሎለታል፡፡

የዳርፉር ጦርነትን በሱዳን ታሪክ ጥቁር ዘመን ሲሉ የጠሩቱን የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች ፍርድ ቤት ዋና ዐቃቤ ሕግ ካሪም ካን መቀመጫውን በኔዘርላንድ ያደረገው ተቋም ጠንካራ የክስ መዝገብ ለማደራጀት እንዲያስችለው መረጃ ለማሰባሰብ በሱዳን ቢሮ ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ዋና ዐቃቤ ሕግ ካሪም ክኻን ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ያወጣባቸውን ሁሉንም ግለሰቦች ጉዳይ ጨምሮ ከሱዳን የሽግግር መንግሥት ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በትላንትናው እለት ነው የተናገሩት፡፡

የ77 አመቱ አል በሽር በዳርፉር ተፈጽመዋል በሚል በተከሰሱባቸው የጅምላ ፍጅት፣ የጦር ወንጀሎች፣ በሰብዓዊነት የተፈጸሙ ወንጀሎች ምክንያት ለአስር ዓመታት ገደማ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ፍርድ ቤቱ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

አል-በሺር በሥልጣን ላይ ሳሉ ፈጽመዋቸዋል በተባሉ አምስት ወንጀሎች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከሶስት አመታት በፊት ከሥልጣን ወርደው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሱዳን ፕሬዝዳንት ሁለት ጊዜ በዚሁ ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዋል። ሌሎች ሁለት ረዳቶቻቸውም ተመሳሳይ ክስ አለባቸው።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትረ መርየም አል መሕዲ ከሰሞኑ አገራቸው የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዑመር አልበርሽን ጨምሮ የወቅቱን ሹማምንት ለጦር ወንጀሎች ፍርድ አሳልፋ እንደምትሰጥ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img