Tuesday, October 15, 2024
spot_img

አል በሽር ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሊሰጡ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― ሱዳን የቀድሞውን ፕሬዝደንት ዑመር አል በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ እንድትሰጥ በካቢኔዋ በኩል ውሳኔ ማሳለፏ ተነግሯል።

ሱዳን አል-በሽርን አሳልፋ የምትሰጠው በቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክሶች መሆኑን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም አል መሕዲ ለሚዲያዎች ተናግረዋል።

መርየም አል መሕዲ ከአል በሽር በተጨማሪ ሌሎች የወቅቱ ሹማምንት ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው እንደሚሰጡ ያሳወቁ ቢሆንም መቼ ተፈጻሚ እንደሚሆን ግን የገለጹት ነገር የለም።

የ77 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝደንት በፈረንጆቹ 2003 ላይ በዳርፉር ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በዘር ማጥፋት፣ በጦር ወንጆሎችና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ክሶች ቀርቦባቸዋል።

ሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንቱዋን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ የመስጠት ዜና የመጣው የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ሕግ ከሪም ካን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጋር መገናኘታቸው ከተነገረ በኋላ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img