Monday, October 14, 2024
spot_img

በምሥራቅ ወለጋ ሆሮጉድሩ ዞን ዘጠኝ ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሐምሌ 6፣ 2013 ― በምሥራቅ ወለጋ ሆሮጉድሩ ዞን ኢሙር ወረዳ ልዩ ቦታው ኢላሞ የተባለ አካባቢ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሎ ዋዜማ ረራድዮ ዘግቧል፡፡

እሑድ አመሻሽ ላይ ‹‹የኦነግ ሸኔ›› አባላት ናቸው ያሏቸው ታጣቂዎች ወደ አካባቢው መተው ተኩስ እንደከፈቱባቸው የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በወቅቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በቦታው አልነበሩም ብለዋል። ታጣቂዎቹ አምስት ወንዶችና አራት ሴቶች በድምሩ ዘጠኝ ሰዎችን በጥይት እንደገደሉ ሌሎች ስድስት ሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከዚህ በተጨማሪም ታጣቂዎቹ አራት ሕፃናትን ከአካባቢው ይዘው ተሰውረዋል፡፡ የሟቾቹ አስከሬን ትላንት ተነስቶ ሥርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙም ተሰምቷል፡፡

ነዋሪዎቹ የአካባቢው ሚሊሻና ልዩ ሀይል ባለመኖሩ ለጥቃት ተጋልጠናል ባይ ናቸው።

መልክአ ምድሩ ሸለቆ እና ጫካ እንደሆነ የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዋች ታጣቂዎቹ የመንግስት የፀጥታ አካላት በቦታው አለመኖራቸውንና ጨለማን ተገን አርገው በተደጋጋሚ ግድያና ዘረፋ እያደረሱብን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የሚመለከተው የኦሮሚያ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን መግለጹም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img