Sunday, October 13, 2024
spot_img

ለመምህራን በኪራይ ተሰጥቷቸው የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው ተወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― ለመምህራን በኪራይ ተሰጥቷቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው የከተማ አስተዳደሩ ወሰነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ2009 ለመምህራን በኪራይ ተላልፎላቸው የነበረውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ቀደም ሲል የነበረው ካቢኔ በወሰነው መሰረት በወቅቱ ዋጋ እንዲተላለፍላቸው ወሰኗል።

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ለተለያዩ ተቋማት የተላለፉ የ40/60 እና 20/80 ቤቶችም የከተማ አስተዳደሩ ካለበት ከፍተኛ የወለድ ጫና ለማዳን ተቋማቱ ሙሉ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ እንዲተላለፉ ውሳኔ ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪን ዋቤ አድርጎ ኢቢሲ ዘግቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img