Thursday, October 10, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2 ሺሕ በላይ የ20/80 እና 40/60 የጋራ ቤት ዕጣ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሰኔ 2፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ በዚህ ሳምንት መገባደጃ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ሊያወጣ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ዕጣ የሚወጣበት እያንዳንዱ የቤት ዓይነት ባይገለጽም፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ቤቶች ለዕጣ ተዘጋጅተዋል፡፡

ምንም እንኳን ሁከትና ብጥብጥን አስከትሎ የነበረውና በወቅቱ ምክትል ከንቲባ በነበሩት ታከለ ኡማ አማካይነት የካቲት 27፣ 2011 ዕጣ ወጥቶባቸው የነበሩ 51 ሺሕ 299 የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለዕድለኞቹ ቁልፍ ተሰጥቶ ያልተጠናቀቀ ቢሆንም፣ አሁንም ዕጣ መውጣቱ በተለይ ለ1997 ተመዝጋቢዎች ትልቅ ተስፋ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በአጠቃላይ በ2005 650 ሺሕ ዜጎች የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማግኘት ተመዝግበው የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ200 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ያለሟቋረጥ እየቆጠቡ ያሉ ናቸው፡፡ በ1997 ዓ.ም. የተመዘገቡና ዕጣ እየጠበቁ የሚገኙት ነዋሪዎች 18,000 ናቸው፡፡

በተለይ በ1997 ተመዝግበው ላለፉት 16 ዓመታት በመጠባበቅ ላይ ያሉት ነዋሪዎች ሰሞኑን ይወጣል በተባለው ዕጣ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚካተቱም ተጠቁሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img