Monday, October 7, 2024
spot_img

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትንና እጩ የፖሊስ መኮንኖችን አስመረቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 30፣ 2013 ― የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በደብረ ማርቆስ በሚገኘው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ያሠለጠናቸውን ምልምል ልዩ ሀይል ፖሊስ አባላትንና እጩ የፖሊስ መኮንኖችን አስመርቋል፡፡

ምልምል ፖሊሶቹ በ7ኛ ዙር መርኃ ግብር የሰለጠኑ ሲሆን፣ እጩ የፖሊስ መኮንኖቹ ደግሞ በ5ኛ ዙር የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በዛሬ ምርቃት የመረጃና የክትትል ፖሊሶችም ተመርቀዋል።

ተመራቂዎቹ በሥልጠና ቆይታቸው ልዩ ልዩ ፖሊሳዊ እውቀትና ክህሎቶችን መቅሰማቸውም ተገልጿል፡፡

በሥነ ሥርአቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሰማ ጥሩነህ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ ተገኝተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img