Saturday, November 23, 2024
spot_img

የእነ ስብሐት ነጋ የቅድመ ምርመራ ምስክሮች አሰማም ሂደት በዝግ ችሎት እንዲካሄድ ተወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ በእነ አቶ ስብሐት ነጋ መዝገብ የቅድመ ምርመራ የምስክሮች አሰማም ሂደት በዝግ ችሎት እና የምስክሮች ሥምና አድራሻቸው ሳይጠቀስ እንዲካሄድ ዛሬ አርብ ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ዐቃቤ ሕግ ‹‹ለምስክሮች ጥበቃ አድርጌያለሁ›› ማለቱን ተከትሎ በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን መቃወሚያ ከመረመረ በኋላ ነው።

በዐቃቤ ሕግ በኩል የተነሳው የምስክሮች ጥበቃ ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፤ ከቀረቡለት ሥስት የምስክር አሰማም ሂደቶች ሁለቱን መቀበሉን በውሳኔው አመልክቷል።

ተቀባይነት ካገኙት የምስክር አሰማም ሂደቶች የመጀመሪያው ማንኛውም ሚዲያ እና ታዳሚ ሳይገባ በዝግ ችሎት የቅድመ ምርመራ ምስክሮች የሚሰሙበት ነው።

የምስክሮች ሥም እና አድራሻ ለተጠርጣሪዎች ሳይጠቀስ የምስክሮች ቃል የሚሰማበት ሁለተኛው አካሄድም እንዲሁ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አግኝቷል። ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው የምስክር አሰማም ሂደት፣ ምስክሮች በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዲመሰክሩ በሚል በዐቃቤ ሕግ የቀረበውን መሆኑን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img