Monday, November 25, 2024
spot_img

አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ታመናል በማለታቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ታኅሣሥ 21 2014 ― በእስር ላይ የሚገኙት የሕወሓት ሰው አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ታመናል በማለታቸው ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ተነግሯል፡፡

ጉዳያቸው በሚታይበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ታመናል በማለታቸው ያልቀረቡት አቶ ስብሐት ነጋ፣ አቶ ባዲ ዘሙ፣ አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣ ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና ቴድሮስ ሐጎስ መሆናቸው ነው የተነገረው፡፡

የማረሚያ ቤት ተወካይ አምስቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጧቸው ለችሎቱ ማስረዳታቸውም ተገልጧል፡፡

የመዝገቡ ቀሪ ተከሳሾች ማለትም ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ አምባሳደር ዐባይ ወልዱ፣ ዶ/ር አብርሐም ተከስተ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣ አምባሳደር አዲስአለም ባሌማ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገ/ እግዚአብሔርን ጨምሮ 16 ተከሳሾች በችሎት ተገኝተዋል።

ችሎቱ ዛሬ በተከሳሾች መዝገብ ላይ የተሰየመው የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ውጤት ለመጠባበቅ እና ሱር ኮንስትራክሽንን ጨምሮ በክሱ የተካተቱ ድርጅቶች መጥሪያ እንዲደርሳቸው የተሰጠውን ትእዛዝ ማረጋገጫ ውጤት ለመጠባበቅ እንዲሁም በ44ኛ ተከሳሽ ለምርመራ የተያዘብኝ ሰነዶች ይመለሱልኝ ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ነበር።

ችሎቱ ስራውን እንደጀመረ ዶ/ር አብርሐም ተከስተ ሁለት ጠበቆቻችን ታስረዋል ቀሪዎቹም ከፍተኛ ስጋት ስላለባቸው አልመጡም ስለዚህ ጠበቆቻችን በሌሉበት ጉዳያችን ሊታይ አንፈልግም ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ያሉ ቢሆንም፣ የተከሳሾች አንደኛው ጠበቃ ክፍላይ መሐሪ ግን ዘግይተው በችሎት ተገኝተዋል።

ይሁንና ጠበቃው ባለፈው ቀጠሮ በእስር ላይ ይገኛል በተባለው አንደኛው ጠበቃ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ላይ የክስ መቃወሚያ መኖሩን ተከትሎ የክስ መቃወሚያውን አግኝተው በተረጋጋ መልኩ ተወያይተው ማቅረብ አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል።

አዲስ መቃወሚያ ለማቅረብ የታሰሩት ጠበቆች ሐሳብ አካትቶ አሟልተው ለማቅረብ እንደሚቸግራቸው በመግለጽ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የክስ መቃወሚያውን ብቻ ለመጠባበቅ ለጥር 30፣ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከተከሳሾቹ መካከል የተወሰኑት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ማስታወሻ ደብተራችን ለምርመራ እየተወሰደብን በመሆኑ ማስታወሻ ደብተር እና በቋንቋችን ስልክ ማውራት እንዲፈቀድልን ይታዘዝልን በማለት አመልክተዋል፡፡

ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በበኩላቸው በማረሚያ ቤት በተለያዩ ቦታዎች የታሰርን መሆኑን ተከትሎ ተሰብስበን ለመወያየት ባለመቻላችን ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የተሰጠንን የክስ ቻርጅ ሲዲን ለመመልከት ኮምፒዩተር ይፈቀድል ሲሉም አመልክተዋል።

በተነሱ አቤቱታዎች ላይ ብቻ ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለታሳስ 27 ፣ በተነሱ አቤቱታዎች ላይ ብቻ ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 27፣ 2014 የቀጠረ ሲሆን፣ ማረሚያ ቤቱም አቤቱታ ያቀረቡ ተከሳሾችን ብቻ ነጥሎ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img