Friday, November 22, 2024
spot_img

ከሰዳል ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠየቁ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_text_color=”#242E3F” text_font_size=”18px” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሰዳል ወረዳ ተፈናቅለው ሰሞኑን አሶሳ ከተማ የገቡ ነዋሪዎች መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

ተፈናቃዮቹ ቀያቸውን ጥለው ወደ አሶሳ የተፈናቀሉት የዛሬ ሳምንት ሚያዚያ 12 2013 በታጠቁ ሽፍቶች ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ነው፡፡

ወደ 200 ኪሎ ሜትር በእግራቸው ተጉዘው አሶሳ መግባታቸውን የተነገረው ተፈናቃዮቹ፣ በጥቃቱ ወቅት የጉሙዝ ማኅበረሰብ ከለላ በመስጠት ከሽፍታው ቡድን እንደታደጋቸውና የክልሉ ልዩ ኃይል ከጥቃት ሊከላከለን ጥረት አድርጓል ብለውኛል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በወረዳው የተፈጠረውን ጉዳይ አስመልክቶ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ ሐሚድ ‹‹ሽፍታ›› ያሉት ታጣቂ ቡድን ‹‹ተስፋ በመቁረጥ ያለውን ኃይል አሟጦ በመጠቀም ጥቃቱን ማድረሱን›› አመልክተዋል።

በጥቃቱ የተቃጠሉ መኖሪያ ቤቶች እንዳሉ ያመለከቱት ምክትል ኃላፊው፣ የተጎዱና የተፈናቀሉትን ትክክለኛ ቁጥር የማጣራት ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ክስተት የክልሉ መንግሥት ማዘኑን የገለጹት አቶ ሙሳ ሽፍታው ቡድን በየቦታው በሃገር መከላከያ እና በክልሉ ልዩ ሃይል የሚደርስበትን ጥቃት መቋቋም አቅቶት እየተበታተነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወረዳው የተሰማራው የጸጥታ ሃይል በሽፍታው ቡድን ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠቁመው፤ ሽፍታው ከመንግስት አቅም በላይ አይሆንም ያሉ ሲሆን፣ ቡድኑን የማስወገድ እንቅስቃሴ ከቀናት በኋላ ውጤት ይገኛል በለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡

ክልሉ የሁሉም ብሄረሰቦች መገኛ መሆኑን በመገለጽም፣ በአካባቢው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም እና ተፈናቃዮች ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮችን ለመደገፍ ከአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጋር የተጀመረ ጥረት መኖሩን አቶ ሙሳ አስረድተዋል።

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img