Monday, October 7, 2024
spot_img

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በሠዓታት ውስጥ ከሥልጣናቸው ሊለቁ መሆኑ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ታኅሣሥ 13 2014 ― በቅርቡ በመፈንቅለ መንግስት ከሥልጣናቸው ተወግደው ዳግም የተመለሱት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣቸውን ሊለቁ መሆኑን የዘገበው ሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡

የዜና ወኪሉ ሐምዶክ ሥልጣናቸውን ሊለቁ መወሰናቸውን የተናገሩት ለሚቀርቧቸው ጥቂት ፖለቲከኞች እና ምሁራን እንደሆነ ነው ያመለከተው፡፡

በመስከረም ወር መገባደጃ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን በሚመሩት የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ተወግደው የነበሩት ሐምዶክ፣ እንደገና ወደ ሥልጣናቸው የተመለሱት ከወር በፊት እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ሐምዶክ ወደ ሥልጣን ሲመለሱ ከጦሩ ጋር ስምምነት ፈርመው የነበረ ቢሆንም፣ ይህን ስምምነት ሱዳናዊያን እና የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ከጦሩ ጋር የፈረሙትን አዲስ የሽግግር ስምምነት በጽኑ እየተቃወሙት ይገኛሉ።

ሱዳን አሁንም የአደባባይ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች የምትገኝ ሲሆን፣ ባሳለፍነው እሑድ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የአገሩ ዜጎች አደባባይ ውለዋል፡፡ በካርቱም ውስጥ በተደረገው ሰልፍ ተቃዋሚዎች የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ የሆኑት የጄነራል ዐብደልፈታህ አል ቡርሃን መቀመጫ ወደሆነው ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት አቅንተው ‹‹ሕዝቡ ጠንካራ ነው፣ ማፈግፈግ የለም›› በማለት ቡርሃን ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ከዚህ ቀደም አንድ የዶክተሮች ቡድን ባወጣው መረጃ ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ቢያንስ 45 ሰዎች በሱዳን ፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል።

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img