Friday, November 22, 2024
spot_img

በሱዳን በተቃውሞ ላይ የተለቀቀ አስለቃሽ ጭስ አነጋጋሪ ሆነ

  • የአስለቃሽ ጭሱ በተተኮሰበት ወቅት በቅርቡ በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት ሰበብ ታስሮ የነበረ የተቃዋሚ መሪ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 9 2014 ― የፖለቲካ መረጋጋት በራቃት ሱዳን በትላንትናው እለት ተቃውሞ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የተለቀቀ አስለቃሽ ጭስ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

በመዲናዋ ካርቱም በተካሄደውና ሺሕዎችን እንዳሳተፈ የተነገረለት ተቃውሞ የተዘጋጀው በሱዳን ነጻነት እና ለውጥ ንቅናቄ ነበር፡፡

የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የተለቀቀው አስለቃሽ ጭስ መነጋገሪያ የሆነው ሰልፈኞቹ በነበሩበት አካባቢ የጸጥታ አካላት ባለመታየታቸው መሆኑን የሬውተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የአስለቃሽ ጭሱ በተለቀቀበት ወቅት ታዋቂው የሱዳን ተቃውሞ ፖለቲካ አራማጅ ኻሊድ ዑመር የሱፍ ንግግር እያደረገ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ፖለቲከኛው በቅርቡ በአገሪቱ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውሎ የተለቀቀ ነው፡፡

ክስተቱን ተከትሎ የተናገረው ኻሊድ፣ ጥይትም ሆነ አስለቃሽ ጭስ ቢተኩስ ፀጥ ሊያሰኙን አይችሉም ብሏል፡፡

በሱዳን በመስከረም ወር በተካሄደው መፈንቅለ መንግስት የአገሪቱ ጦር የሲቪል አስተዳደሩን መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክን በማሰር አስተዳደሩን መበተኑ ይታወሳል፡፡ ኋላም ጦሩ ከተለያዩ አካላት በበረታበት ተቃውሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ሥልጣናቸው ቢመልስም፣ የጦሩን ተግባር ተቃውመው አደባባይ የዋሉ ሰልፈኞች አሁንም ድረስ ተቃውሟቸውን ሊያቆሙ አልቻሉም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img