Thursday, November 28, 2024
spot_img

አሶሺየትድ ፕረስ በኢትዮጵያ የሚገኘው ዘጋቢዬ ታስሮብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 8፣ 2014 ― መቀመጫውን አሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገው አሶሺየትድ ፕረስ የተሰኘው የብዙኃን መገናኛ በኢትዮጵያ የሚገኘው የቪዲዮ ዘጋቢው አሚር አማን ኪያሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ታስሮብኛል ብሏል፡፡

የብዙኃን መገናኛው አሚር አማን ኪያሮ ታስሯል ያለው ኅዳር 19፣ 2014 ሲሆን፣ ጋዜጠኛው ዘገባ ሠርቶ ወደ መኖሪያው አዲስ አበባ ሲመለስ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከትላንት በስትያ ታኅሣሥ 6፣ 2014 መግለጫ ያወጣው ፖሊስ በበኩሉ ጋዜጠኛውና ባልደረቦቹ የታሰሩት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በሽብርተኝነት የተፈረጀው በመንግስት ሸኔ የሚባለውን እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራውን ቡድን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነው ብሏል፡፡

ፖሊስ ከአሚር አማን በተጨማሪ ከሚዳ ቀኝ ወረዳ እስከ ኬንያ ድረስ ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው ቡድኑን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበር በማለት በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ቶማስ እንግዳ እና አዲሱ ሙሉነህ የተባሉ የሚዲያ ባለሞያዎች ናቸው፡፡

ዘጋቢዬ ታስሯል ያለው የአሶሺየትድ ፕረስ ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ጁሊ ፓሲ ፖሊስ ጋዜጠኛው ኢነግ ሸኔን የማስተዋወቅ ሰርቷል ማለቱን በማጣጣል፣ መንግስት ጋዜጠኛውን እንዲለቀው ጠይቀዋል፡፡

በትላናትናው እለት መግለጫ ያወጣው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ በኢትዮጵያ ከጥቅምት 23፣ 2014 ጀምሮ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ 14 ጋዜጠኞች መታሠራቸውን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አስር ቀናት ከታሰሩ ሚዲያ ላይ ከሚሠሩት መካከል እያስጴድ ተስፋዬ ከኡቡንቱ ቲቪ፣ ታምራት ነገራ ከተራራ ኔትወርክ እና መዐዛ መሐመድ ሮሃ ከተሰኘ የበይነ መረብ ሚዲያ ይጠቀሳሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img