Sunday, October 6, 2024
spot_img

ዳግሎ አውሮፓ እና አሜሪካ የሱዳንን መንግሥት ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የላቸውም አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ኅዳር 24፣ 2014 ― የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ምክትል መሪ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ ወይም በሥፋት በሚታወቁትበት መጠሪያቸው ሄሜቲ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ መንግሥታችንን ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የላቸውም ብለዋል፡፡

ሄሜቲ አውሮፓ እና አሜሪካ መንግታቸውን ከመደገፍ ውጭ አማራጭ የላቸውም ለማለታቸው በሱዳን ችግር ከተፈጠረ በተለይ አውሮፓ በሱዳን ስደተኞች ሊጥለቀለቅ ይችላል የሚል ምክንያት አስቀምጠዋል ሲል የዘገበው ሚድል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡

ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎን ያቀፈው የሱዳን የጦር ከወር በፊት ዳግም የመንግሥት ግልበጣ ካደረገ በኋላ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ተቃውሞ በርትቶበታል፡፡

ጀነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን የሚመሩት የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግስት ሲያደርግ ያሰራቸውን አብደላ ሐምዶክን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ቢመልስም፣ የሚደረገው ተቃውሞ ጋብ ሊል አልቻለም፡፡

ሐምዶክ ወደ ሥልጣን የጠመለሱት፣ ከሱዳን ጦር መሪው ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ስምምነት መፈረማቸውን ተከትሎ ነበር፡፡

ሬውተርስ የዜና ወኪል ከሁለት ቀናት በፊት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሐምዶክ እነዚህ ስምምነቶች በአግባቡ የማይተገበሩ ከሆነ ሥልጣናቸውን ሊለቁ ይችላሉ ብሏል፡፡

ሐምዶክ ስምምነቱ እንዲተገበር ይፈልጋሉ ቢባልም፣ ባለፈው ማክሰኞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን የሱዳን ጦር ከሃገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል ለመጠየቅ ወደ አደባባዮች ወጥተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በአደባባይ ይዘዋቸው በታዩ መፈክሮች የጦሩን ድርጊት በማውገዝ፣ ስልጣን ለህዝብ ተላልፎ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከጦሩ ጋር የሚደረግ ‹‹ስምምነትም ሆነ አጋርነት›› እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img