Friday, November 22, 2024
spot_img

ጄነራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ 54 ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ጋር በመሆን እንዲያቀርባቸው ትዕዛዝ ተሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 23 2014 ― ጄነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ እና ታደሰ ወረደን ጨምሮ 54 ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ጋር በመሆን እንዲያቀርባቸው ትዕዛዝ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ዓቃቤ ሕግ ግለሰቦቹን በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ሕወሓት አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ህገ ወጥ ወታደራዊ ቡድን በማደራጀትና በመምራት በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ሰራዊት በሰሜን ዕዝ እንዲሁም በአማራና በአፋር ክልሎች ጥቃት ማድረስ በሚል በሽብር ወንጀል ክስ እንደመሠረተባቸው ይታወሳል፡፡

ክስ የተመሰረተባቸው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ጄነራል ጻድቃን ገ/ ተንሳይ፣ ሜጀር ጄነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ብርጋዴር ጄነራል ምግባይ ኃይሌ፣ ሜጀር ጄነራል ማሾ በየነ፣ ሀዱሽ አበበ እና ቢኒያም ተወልደን ጨምሮ 74 ናቸው፡፡ ሆኖም ከነዚህ ውስጥ 20 የሚሆኑት በፖሊስ በቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡

ጉዳያቸውን የሚመለከተው ችሎት ለዛሬ የተሰየመው፣ ክስ ያልደረሳቸው 3 ተከሳሾች ክሱ እንዲደርሳቸው የሰጠውን ትእዛዝ ለመመልከት እንዲሁም በቁጥጥር ስር የዋሉ አጠቃላይ 20 ተከሳሾችን ማረሚያ ቤት እዲያቀርባቸው የሰጠውን ትእዛዝ ውጤት ለመጠባበቅ ነበር።

ነገር ግን በቂሊንጦ የሚገኙ 3 ተካሳሾችን ጨምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት ጋር 20 ተከሳሾች ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ያልቀረቡበትን ምክንያት ማረሚያ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ተከሳሾችንም በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ በማዘዝ ለታኅሣሥ 26፣ 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img