Sunday, November 24, 2024
spot_img

የሱዳኑ ጠ/ሚ ከጦሩ ጋር የገቡት ስምምነት የማይተገበር ከሆነ ሥልጣናቸው ሊለቁ ይችላሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 23፣ 2014 ― ከሳምንታት በፊት በአገሪቱ ጦር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ከሥልጣናቸው ተነስተው ዳግም በደረሱት አዲስ ስምምነት የተመለሱት ዐብደላ ሐምዶክ፣ ከጦሩ ጋር የገቡት ስምምነት የማይተገበር ከሆነ ሥልጣናቸው ሊለቁ ይችላሉ ተብሏል፡፡

የሱዳን ጦር መሪው ጀነራል ዐብዱልፈታህ አልቡርሃን በሀገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ ሦስት ሳምንታት መልሰው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ ጋር መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡  

ሁለቱ የአገሪቱ ባልስልጣናት ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና አንድ ወጥ የሆነ የሱዳን ጦር መመስረት፣ የሱዳንን ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅ፣ የሽግግር ጊዜውን የሚመራውን ሕገ መንግሥታዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ አሰራሮችን መወሰን የሚሉት ይገኙበታል።

ሬውተርስ የዜና ወኪል ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሐምዶክ እነዚህ ስምምነቶች በአግባቡ የማይተገበሩ ከሆነ ሥልጣናቸውን ሊለቁ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

ሐምዶክ ስምምነቱ እንዲተገበር ይፈላጋሉ ቢባልም፣ ከሁለት ቀናት በፊት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን የሱዳን ጦር ከሃገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል ለመጠየቅ ወደ አደባባዮች ወጥተዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በአደባባይ ይዘዋቸው በታዩ መፈክሮች የጦሩን ድርጊት በማውገዝ፣ ስልጣን ለህዝብ ተላልፎ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከጦሩ ጋር የሚደረግ ‹‹ስምምነትም ሆነ አጋርነት›› እንደማይኖር ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img