Wednesday, November 27, 2024
spot_img

በወለጋ መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውን ቡድን ኢላማ ያደረገ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 21፣ 2014 ― በምሥራቅ ወለጋ ዞን መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የሚለውን ቡድን ኢላማ ያደረገ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ ተነግሯል፡፡

ጥቃቱን በተመለከተ በመንግሥት በኩል ይፋ የተደረገ ነገር ባይኖርም፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሚለው ቡድን ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ጥቃቱ የስልክ ኔትወርክ ከጠፋ በኋላ የተፈጸመ መሆኑን ነግሮኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

ቃል አቀባዩ በሂሊኮፕተር ተፈጽሟል ያለው የአየር ጥቃት በምሥራቅ ወለጋ ዞን ኢባንቱ ወረዳ መጀመሩን መግለጹም በዘገባው የተመላከተ ሲሆን፣ ንጹሐን ሰለባ ስለመሆናቸውም መናገሩ ሠፍሯል፡፡  

‹የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት› የተባለው ቡድን ታጣቂዎች በምሥራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ እንዲሁም በጉጂ ዞኖች እንደሚንቀሳቀስ የሚነገር ሲሆን፣ በሥፍራዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ለሚፈጸሙ ጥቃቶች መንግሥት ቡድኑን ተጠያቂ ያደርጋል።

ቡድን በክልሉ በንጹሃን ዜጎች እና በአካባቢ ባለስልጣናት ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶችና ግድያዎች ጋር በተደጋጋሚ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img