Sunday, October 6, 2024
spot_img

በማረሚያ ቤት የሚገኙት የነ አቶ በቀለ ገርባን ደኅንነት በተመለከተ ስጋት እንደገባው ልጃቸው ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 15 2014 ― በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ አመራር የሆኑት የአቶ በቀለ ገርባ እና አብረዋቸው የሚገኙት አቶ ጀዋር መሐመድ እንዲሁም ሌሎችም ታሳሪዎችን ደኅንነት በተመለከተ ስጋት እንደገባው የአቶ በቀለ ልጅ የሆነው ሳሙኤል በቀለ ገልጧል፡፡

ሳሙኤል በቀለ እንደገለጸው፣ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጥቅምት 9፣ 2014 በርካታ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ እና ሦስት ሲቪል ለባሾችን የጫነ ተሽከርካሪ ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እውቅና ውጭ ወደ ውስጥ ዘልቀው እነ ጀዋር መሐመድ ወዳሉበት እንዲወስዷቸው ጠይቀዋል፡፡ ሆኖም የማረሚያ ቤቱ ጥበቃዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ በመከልከላቸው ውዝግብ በመፈጠሩ፣ የእለቱ ተረኛ ኃላፊ በመምጣት ሰዎቹ የማረሚያ ቤቱን ቅጽር ለቀው እንዲወጡ አድርጓል፡፡

የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወደ ማረሚያ ቤቱ የዘለቁት ግሰለቦች ከብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት (ኢንሳ) የሄዱ መሆናቸውን ባደረግነው ማጣራት ደርሰንበታል ብሏል፡፡  

ከዚህ ክስተት በኋላ የታሳሪዎቹ ደኅንነት እንዳስጨነቃቸው የገለጸው ሳሙኤል በቀለ፣ በአሁኑ ጊዜ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎቹ እንደተቀየሩና ኃላፊውንም የማንሳት ሙከራ መኖሩን ጠቁሟል፡፡

በመሆኑም መንግስት እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባቱን ጨምሮ የታሳሪዎቹን ጉዳይ እንዲመለከቱትና ደኅንነታቸው እንዲረጋገጥ ጠይቋል፡፡ የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ሳሙኤል በቀለ ላቀረበው የታሳሪዎች የደኅንነት ስጋት ማሳሰቢያ እስካሁን ድረስ በማረሚያ ቤቱም ሆነ በመንህስት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች ታሳሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በ2012 ሰኔ ወር ላይ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img