Sunday, November 24, 2024
spot_img

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኮምቦልቻ የሚገኙ መጋዘኖቼ ተዘርፈዋል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 14፣ 2014 ― የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሕወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ኮምቦልቻ ውስጥ ያሉት የሰብዓዊ እርዳታ ማከማቻ መጋዘኖቹ መዘረፋቸውን አስታውቋል።

የፕሮግራሙ ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ድርጅት በአማራ ክልል ኮምቦልቻ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያቀርብ ፍቃድ አግኝቷል ያሉ ሲሆን፣ ባደረገው ቅድመ ግምገማ መሠረትም በርካታ ንብረቶቹ መውደማቸውን እና መጋዘኖች ውስጥ የነበረ እህል መዘረፉንም ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ይህን ዝርፊያ ማን እንደፈጸመው እና መቼ እንደተፈጸመ የገለጹት ነገር የለም።

ቃል አቀባዩ ቶምሰን ፊሪ፤ የዓለም ምግብ ድርጅት መጋዘኖች መዘረፍ ማለት የዓለም ምግብ ፕሮግራምና አጋሮቹ የሚያቀርቡት የእርዳታ መጠን የተገደበ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።

ይህ ቢሆንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሁን ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ጭምር እርዳታ እየሰጠ እንደሆነና ከዛሬ ጀምሮ በኮምቦልቻና ደሴ ከተሞች ለ450 ሺህ ሰዎች እርዳታ መስጠት እንደሚጀምር ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ እንቅስቃሴውን እንዲያከብሩ ጠይቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img