Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳን ዋንኛው የተቃዋሚ ጥምረት ከጦሩ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ስምምነት እውቅና እንደማይሰጥ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 13 2014 ከሦስት ሳምንት በፊት መፈንቅለ መንግስት ያስተናገደችው ሱዳን፣ በትላንትናው እለት በቁም እስር ላይ በነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብደላ ሐምዶክ፣ በአገሪቱ ጦር አዛዥ፣ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ታጣቂ ቡድኖች መካከል መድረሳቸው ተነግሮ ነበር፡፡

ነገር ግን የአገሪቱ ዋንኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የነጻነት እና ለውጥ ኃይል ከጦሩ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ስምምነት እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡ እንደ ጥምረቱ ከሆነ በሱዳን መፈንቅለ መንግስቱን ተከትሎ በጦሩ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ ይቀጥላል፡፡

በትላንትናው እለት በዋነኛነት በጦር አዛዡ ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሀን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብዱላህ ሃምዶክ የተፈረመው ስምምነት በ14 ጉዳዮችን ዙሪያ ያተኮረ ስለመሆኑ ተነግሮለታል፡፡

መሪዎቹ ከተስማሙባቸው ጉዳዮች መካከል ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና አንድ ወጥ የሆነ የሱዳን ጦር መመስረት፣ የሱዳንን ግዛታዊ አንድነት ማስጠበቅ፣ የሽግግር ጊዜውን የሚመራውን ሕገ መንግሥታዊ፣ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ አሰራሮች መወሰን የሚሉት ይገኙበታል።

ስምምነቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላህ ሐምዶክን ወደ ቀደመ ሥልጣናቸው የመለሰ ሲሆን፣ ከስምምነቱ በኋላ ሐምዶክ ባደረጉት ንግግር አንድነት ለሱዳን አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፣ የአገሪቱን ጥቅም ማስጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

‹‹የተፈረመው ስምምነት ለሳምንታት የተሰራ የጠንካራ ስራ ውጤት ነው›› ያሉት ሐምዶክ፣ ‹‹ሱዳን ምንም መመለስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ብትደርስም መመለስ እንደምትችል ያረጋገጠ ነው›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ሌተናል ጀነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሀን በበኩላቸው ‹‹ዛሬ የተፈረመው ስምምነት የሱዳናውያን የስራ ውጤት ነው፣ ይህ የእውነተኛ ሽግግር ጅማሮ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል።

አል ቡርሃን በመሩት መፈንቅለ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብደላ ሐምዶክ በቁም እስር ላይ መቆየጣቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img