Thursday, October 17, 2024
spot_img

የአማራ ክልልን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት የኢኮኖሚ አቅም ለመመለስ ቢያንስ ሠላሳ ዓመት ሊወስድ ይችላል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ኅዳር 11 2014 በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት ተስፋፍቶ ውድመት ያስተናገደው የአማራ ክልልን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት የኢኮኖሚ አቅም ለመመለስ ቢያንስ ሠላሳ ዓመት ሊወስድ ይችላል ያለው የክልሉ የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ነው።

በጦርነቱ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶበታል የተባለው የአማራ ክልል፣ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት እድገት 22 በመቶ የሚሸፍን ነው።

በክልሉ የገጠመውን ውድመት አድርሷል የተባለው፣ ከሐምሌ ወር 2013 ወዲህ ወደ አማራ የተስፋፋው የሕወሓት ኃይል ነው፡፡ የአማራ ክልል የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ አንሙት በለጠን ጠቅሶ ሪፖርተር እንደዘገበው፣ ሕወሓት በተቆጣጠራቸው የክልሉ አካባቢዎች በግብርር ዘርፍ ብቻ አውድሞታል የተባለው 260 ቢሊዮን ብር ተገምቷል፡፡

በግብርናው ዘርፍ በአሁኑ ጊዜ ገበሬዎች ምንም ዐይነት የእርሻ በሬም ሆነ የግብርና መሳሪያዎች እንደሌላቸው የገለጹት ኃላፊው፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉም ቢሆን እንደ አዲስ ከዜሮ እንደሚጀምር አመልክተዋል፡፡

በአማራ ክልል የደረሰውን ውድመት በድጋሚ ለመተካት የክልሉ መንግስት የሐብት ማሰባሰብ ለማካሄድ እቅድ መያዙንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

አንድ ዓመት በተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት በአማራ ክልል በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት አስተናግዷል ከተባሉት የኢንዱስትሪ እና የግብር ዘርፎች ተጨማሪ በርካታ የጤና እና የትምህርት መሠረተ ልማቶ መውደማቸው ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img