Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ረዳት ሚኒስትር ዐብደላ ሐምዶክን ማግኘታቸውን አስታወቁ

 

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 7 2014 ― የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ በሱዳን በቁም እስር ላይ የሚገኙትን የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ዐብደላ ሐምዶክን ማግኘታቸውን አስታወቀዋል፡፡

ረዳት ሚኒስትሩ በሱዳን ለሦስት ቀናት ባደረጉት ጉብኝት ዐብደላ ሐምዶክን ሲገኙ፣ ‹‹የሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደነበረበት መመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች›› ላይ ስለመወያየታቸው በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሬውተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ሞሊ ፊ፣ በአገሪቱ የሚካሄደውን መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት የጦር አዛዡ ዐብደልፈታህ አል ቡርሐንንም አግኝተዋል።

መፈንቅለ መንግስት አድራጊው ሌተናል ጄነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሐን አዲስ ምክር ቤት መስርተው ራሳቸውን ደግሞ መሪ አድርገው መሰየማቸው ይታወቃል፡፡

ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሐን ይህን ምክር ቤት ያቋቋሙት መፈንቅለ መንግሥቱን ለመቀልበስ ከአገር ውስጥ እና ከዓለም አቀፍ አካላትም ጫናው በበረከተበት ወቅት ነው፡፡

በሱዳን መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም የሚካሄደው ተቃውሞ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፣ አንዳንድ ባልደረቦቻቸው የታሰሩባቸው ጋዜጠኞች ወታደራዊውን መንግሥት በመቃወም ትላንት ማክሰኞ ሰልፍ አድርገዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img