Sunday, November 24, 2024
spot_img

አንዲት እናት ላይ በልጇ ፊት ድብደባ የፈጸሙት ሁለት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ከሥራ መባረራቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 7 2014  በመስከረም ወር መገባደጃ በአዲስ አበባ ከተማ ጀሞ ሚካኤል በሚባል አካባቢ አንዲት እናትን በልጇ ፊት ዘግናኝ ድብደባ የፈጸሙት ሁለት የፖሊስ አባላት ከሥራ መባረራቸው ተሰምቷል፡፡

በወቅቱ ሰሚራ በተባለችው የልጅ እናት ላይ ድብደባው ሲፈጸም የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች መሰራጨቱን ተከትሎ ነበር ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡

የፖሊሶቹን ጉዳይ የያዘው የንፋስ ስልክ ላፍቶ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ አባላቱ ለፈጸሙት ድርጊት እያንዳንዳቸው በ3 ሺሕ 300 ብር እንዲቀጡ መወሰኑ የተነገረ ሲሆን፣ ሆኖም የተሰጠው ፍርድ በቂ አይደለም ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለሌሎች ፖሊሶች ማስተማሪያ እንዲሆን በማለት ሁለቱንም ፖሊሶች ከሥራ ማባረሩን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ መናገራቸውን ቁም ነገር ሚዲያ ኢትዮ ኤፍ ኤምን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ባለፈው ዓመት ብቻ በ171 የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች ከሥነ ምግባር ውጭ በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት አቤቱታ እንደቀረበባቸው የተነገረ ሲሆን፣ 29 ያህሉ በከፍተኛ የሥነ ምግባር ችግር ከስራ መባረራቸው ታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img