Tuesday, November 26, 2024
spot_img

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪው ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳገሎ በአል ቡርሃን የተሰጣቸውን አዲስ ኃላፊነት አልቀበልም አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 7፣ 2014 ― በሱዳን መፈንቅለ መንግስት ያደረጉት የጦሩ አዛዡ ሌተናል ጀነራል ዐድዱልፈታህ አል ቡርሃን ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪው ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳገሎ (ሄሜቲ) አዲስ ኃላፊነት ቢሰጡም ሄሜቲ ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡

 

አል ቡርሃን ከሰሞኑ 15 አባላት ያቀፈ አዲስ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት አቋቁመው ራሳቸውን መሪ አድርገው የሾሙ ሲሆን፣ ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳገሎን የአዲሱ ምክር ቤት ምክትል መሪ ሆነው እንደሚያስቀጥሉ ገልጸዋው ነበር፡፡

ይህንኑ ሹመት ተከትሎ ምክትሉ ሐምዳን ዳጋሎ ከሁለት ዓመት በፊት በቀድሞው ፕሬዝዳንት አል በሽር አገዛዝ ቁጥጥር ስር የነበሩ የተለያዩ ጥሪቶችን የሚያስመልሰውን ኮሚቴ እንዲመሩ ኃላፊነት ቢሰጣቸውም እንደማይቀበሉት መናገራቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡

ሄሜቲ አዲሱን ኃላፊነት ለምን እንዳልተቀበሉት የጠቀሱት ነገር አለመኖሩን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ሄሜቲ የመምራት ኃላፊነቱን አልቀበለውም ያሉት ኮሚቴ፣ ሌተናል ጀነራል ዐብደልፈታህ አል ቡርሃን መፈንቅለ መንግስት አድርገው የአገሪቱን የሲቪል አስተዳደር በመበተን፣ በመላው ሱዳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጁ ካገዷቸው መካከል ነው፡፡

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img