Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲፈታ ሕወሓት ሦስት ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟላ መንግስት ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 2፣ 2014 ― አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ከተፈለገ የሕወሓት ኃይሎች ሦስት ቅድመ ሁኔታዎችን ሊያሟሉ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል።

መንግስት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች የህወሓት ኃይሎች ጥቃት እንዲያቆሙ፣ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጡ እንዲሁም የፌደራል መንግስቱን ህጋዊነት እንዲቀበሉ የሚጠይቁ ናቸው። 

ቅድመ ሁኔታዎቹን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ባለፈው ሳምንት ማሳወቃቸውን አቶ ዲና ተናግረዋል። ሁለቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስለ ቅደመ ሁኔታዎቹ የተናገሩት፤ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ማብራራያ በሰጡበት ወቅት ነው።   

ቃል አቃባዩ በዛሬው መግለጫቸው ላይ የጠቀሷቸው ቅድመ ሁኔታዎች “ለድርድር የቀረቡ ናቸው ወይ?” በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፤ ወደ ድርድር ስላልገባን” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ድርድርን በተመለከተ “ተደራደሩ የሚሉ፤ እንድንደራደር የሚፈልጉ ሰዎች አሉ” ሲሉ ሁለቱን ተፈላሚ ወገኖች የማሸማገል ሙከራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በርከት ያሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ታስረዋል መባሉን አስመልክቶ የተናገሩት ዲና፣ “ሰራተኞቹ የታሰሩት፤ የኢትዮጵያን ህግ እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር የተያያዙ ነገሮችን በመጣስ ነው” ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img