Wednesday, November 27, 2024
spot_img

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ መሪ ዴ ክላርክ አረፉ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ኅዳር 2፣ 2014 ― በአፓርታይድ ሥርዓት ስር የመጨረሻው ነጭ የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት ኤፍ ደብሊው ዴ ክላርክ ዜና እረፍታቸው የተሰማው በዛሬው እለት ነው።

በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዴ ክለርክ፣ ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ሥርዓት ወደ ዴሞክራሲ ባደረገችው ሽግግር ወቅት ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ስለመሆናቸው ይነገርላቸዋል።

ዴ ክላርክ ደቡብ አፍሪካን ከአውሮፓውያኑ መስከረም 1989 አስከ ግንቦት 1994 ድረስ መርተዋል።

የነጮች የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓትን ለማብቃት ዋነኛ የተባለውን እርምጃ በ1990 ላይ የፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴ ታጋዩን ኔልሰን ማንዴላን በመፍታት የወሰዱ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላም በ1994 በአገሪቱ የመጀመሪያው የብዝሃ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲካሄድ አድርገዋል።

የቀድሞ ፕሬዝደንት ፋውንዴሽን በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ ኤፍደብሊው ዴ ክላርክ ኬፕታዎን በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ማረፋቸውን አስታውቋል።

በደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ ሥርዓት ውስጥ ለነበራቸው ተሳትፎ እአአ 1992 ላይ ከኔልሰን ማንዴላ ጋር በጋራ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ተቀብለው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img