Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሜን እወቁት አለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 26፣ 2014 ― የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል፡፡ ከትላንት ጥቅምት 25፣ 2014 ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩን የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራርና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡

ፖሊስ ኅብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው፣ አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጠይቋል።

ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደነገገ ስለሆነ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉም ተቋሙ መልዕክቱን ሰዷል፡፡

አዳዲስ ተጨማሪ የደንብ አልባሳቱን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ በሀገራችን የተከሰተውን ለውጥ ተከትሎ መንግስት የፖሊስ ተቋምን ለማዘመን እየሰራ መሆኑን መናገራቸውን የኢቢ ዘገባ ያመለክታል፡፡

አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳት ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው የተቋማችንን ገፅታ ከመገንባት አኳያ ሚናቸው የጎላ በመሆኑ መላው የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት የደንብ ልብስ አጠቃቀምን አስመልክቶ በወጣው መመሪያ መሰረት የደንብ ልብሱን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አመራሮችም መመሪያውን በአግባቡ እንዲያስፈፅሙ አሳስበዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img