Tuesday, November 26, 2024
spot_img

ዐብደላ ሐምዶክ በሱዳን አዲስ ይመሠረታል የተባለውን መንግሥት ለመምራት ተስማምተዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 24፣ 2014 ― በሱዳን ጦር በተመራው መፈንቅለ መንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው የተወገዱት ዐብደላ ሐምዶክ አዲስ የሚመሠረተውን መንግሥት ለመምራት መስማማታቸው ተነግሯል፡፡

ሆኖም የዐብደላ ሐምዶክ ወደ መንግስት መሪነት መመለስ ራሳቸው አስቀምጠዋቸዋል በተባሉ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን አል ዐይን ዘ ናሽናልን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ሐምዶክ አስቀምጠዋቸዋል ከተባሉት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ የሚጠይቁና በሽግግር ጊዜ ህገ መንግስቱ ላይ የተጣለው እገዳ ይነሳ የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በአገሪቱ ጦር አዛዥ ሌተናል ጄነራል ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን በተመራውና ሃምዶክን አሁንም ጭምር ለቁም እስረኝነት በዳረገው መፈንቅለ መንግስት፣ የሃገሪቱን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ካሊድ ዑመር የሱፍን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በጦሩ እና በሲቪል ባለስልጣናቱ መካከል ያለውን ልዩነት ለማረቅ የሚያስችሉ የማሸማገል ጥረቶች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡

በሱዳን የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የአህጉሩ መሪ ድርጅት አፍሪካ ኅብረት አገሪቱን ማገዱ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ጋር በተገናኘ አሜሪካም የምትሰጠውን እርዳታ ማገዷን ማሳወቋ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img