Saturday, November 23, 2024
spot_img

ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም ጤና ድርጅት አለቃነት የቀረቡ ብቸኛው እጩ መሆናቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 19፣ 2014 ― ላለፉት አምስት ዓመታት የዓለም ጤና ድርጅትን በዋና ኃላፊነት የመሩት ኢትዮጵያዊው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለቀጣዩ ዙር ብቸኛ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ድርጅቱ ዛሬ አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዶክተር ቴድሮስ በ28 ሃገራት እጩ ሆነው መቅረባቸውንም ይፋ አድርጓል።

ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖምን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው ዳግም እንዲመረጡ የእጩነት ድጋፍ ከሰጡ ሃገራት መካከል 38 የአውሮፓ ሃገራት የሚገኙበት ሲሆን፣ ከአፍሪካ ኬንያ እና ሩዋንዳ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ለሁለተኛው ዙር እጩነት ባቀረቡት ማመልከቻ ኮቪድ 19 ወረርሺኝ ዓለምን ማንኮታኮቱን ገልፀው፣ በቀጣይ ዙር የሥልጣን ዘመናቸው ዓለማችንን ለመሰል ወረርሺኝ ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጥ ፍላጎታቸው መሆኑን ጠቁመዋል ነው የተባለው።

ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት በፈረንጆቹ 2017 ነበር።

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ፣ በመንግስት በኩል ሕወሓት የጦር መሳሪያ እንዲያገኝና በሌሎች መንገዶች ለመርዳት ሞክረዋል በሚል ውንጀላ እንደቀረበባቸው ይታወሳል። ሆኖም ዶክተር ቴድሮስ ውንጀላውን አስተባብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img