Sunday, September 22, 2024
spot_img

ፌስቡክ ኩባንያውን ሜታ በሚል አዲስ መጠሪያ ሠየመ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 18፣ 2014 ― ግዙፉ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ፌስቡክ ኩባንያውን ሜታ ሲል በአዲስ መጠሪያ ቀይሯል።

ይህንኑ የኩባንያው መስራች ማርክ ዙከርበርግ በበይነ መረብ በተካሄደ ኮንፍረንስ ይፋ አድርገል።

ኩባንያው የሥም ለውጡን ያደረገው ቀጣዩ የበይነ መረብ ዝግመተ ለውጥ ነው በሚባለው ሜታቨርስ ማስፋፊያ ጋር በተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን፣ ኩባንያው ራሱን ከማኅበራዊ ትስስር መድረክነት የላቀ ሥፍራ እንዲኖረው ውጥን መያዙን የሚያመለክት መሆኑም ተነግሮለታል፡፡

የሥም ለውጥ ያደረገው ፌስቡክ፣ በቅርብ ጊዜያት በተለይ ከሚያራምደው ፖሊሲ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ የተለያዩ ትችት አዘል አስተያየቶችን ሲያስተናግድ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img